Filed Data Collector

Abel Tamirat Addis Ababa · ETHIOPIA Posted 2h ago

About this role

የአሽከርካሪዎች ምልመላ እና መረጣ
(Filed Data Collector)

የሥራ ቦታ፦ አዲስ አበባ
የቅጥር ሁኔታ፦ ሙሉ ጊዜ ደመወዝ፦ በወር 10,000
ቦነስ፦ በቀን ከ(500 - 900 ብር)

አሽከርካሪዎችን ወደ ታክሲ የትራንስፖርት አገልግሎት (Ride-hailing) መተግበሪያችን ለመመልመል፣ ለመሳብ እና ለመመዝገብ እንፈልጋለን።

ዋና ዋና ሀላፊነቶች
- በመስክ ጉብኝት አዳዲስ አሽከርካሪዎችን መመልመል።
- ከእጩ አሽከርካሪዎች ጋር በመገናኘት ስለ ድርጅቱ አገልግሎት፣ መስፈርቶች እና የስራ ገቢ እድሎች ማብራራት።
- አሽከርካሪዎችን ማጣራት እና አስፈላጊ ሰነዶችን እንዲሁም ብቃታቸውን ማረጋገጥ።
- አሽከርካሪዎችን በምዝገባ፣ መተግበሪያውን በማስጀመር እና መለያቸውን (Account) በማንቃት ሂደት ማገዝ።
- የዕለታዊ እና ሳምንታዊ የአሽከርካሪዎች ምልመላ ግቦችን ማሳካት።
- ከእጩ አሽከርካሪዎች ጋር በሚደረግ ግንኙነት ድርጅቱን በባለሙያነት ወክሎ መቅረብ።
መስፈርቶች
- ጥሩ የመግባባት ችሎታ።
- በግብ ላይ ያተኮረ/ች እና እራሱን/ሷን ማነሳሳት የሚችል/ምትችል።
- በመስክ ላይ ለመስራት እና ከእጩ አሽከርካሪዎች ጋር ለመገናኘት ዝግጁ የሆነ/ች።
- ስለ ስማርት ስልኮች እና የሞባይል መተግበሪያዎች (Apps) መሰረታዊ እውቀት ያለው/ላት።
- ስለ አዲስ አበባ ከተማ ጥሩ እውቀት ያለው/ላት ቢሆን ይመረጣል።
ማበረታቻዎች (Incentives) የሚከፈሉት ድርጅቱ ባወጣው የማበረታቻ ፖሊሲ መሰረት የተረጋግጡ አሽከርካሪዎችን መሰረት በማድረግ ነው።
እንዴት ማመልከት ይቻላል?ፍላጎቱ ያላችሁ ተወዳዳሪዎች (CV) እና የሞባይል ስልክ ቁጥራችሁን በሚከተለው ስልክ ቁጥር ወይም ቴሌግራም መላክ ትችላላችሁ፦ ስልክ፦ +251921789717 ቴሌግራም፦@desklogic

Skills & tags

  • Communication